★ ዋግምራ ሰቆጣ ነው ተወልጄ ያደኩት።
★ አባቴ የኮንስትራክሽን ሠራተኛ ነው።
እናቴ ደግሞ ጠላ ነው የምትሰራው።
★ እናትና አባቴ ተለያይተው ነው የሚኖሩት።
★ ዩኒቨርስቲ ስማር በትርፍ ሰዓቴ እሰራ ነበር።
★ በሙዚቃ የቤተሰብ ህይወት እቀይራለሁ ብዬ
አስብ ነበር።
★ ያሳለፍኩት ትንሽ ፈተና ጠንካራ እንድሆን
አድርጎኛል።
★ ልጅነት ፣ ወጣትነት ፣ ከማን አንሳለሁ ባይነት
እንድሳሳት አድርጎኛል።
★ ፋና ላምሮት ውድድር ላይ እስከ 5ኛ ደረጃ
አጠናቅቂያለሁ። የአሸናፊዎች አሸናፊ
ውድድር ላይም ተሳትፊያለሁ።
★ የእናቴ ታናሽ ወንድም ከእራሱ ህይወት ላይ
ቀንሶ ሰጥቶኝ እያገዘኝ ነው።
★ የልጄ አባት የፋና ላምሮት ተወዳዳሪ ነበር።
ስሙን መግለፅ ግን አልፈልግም።
★ ሁለታችንም ተዋደን ነበር። ሳረግዝ እሱ ደነገጠ።
25 ዓመቱ ነው። ወጣት ነው። እኔ እንደዛ ነው
የምረዳው።
★ ወጣት ነን። ስሜት አለን። ግን መቆጠብ
ያስፈልጋል።
★ ከልጄ አባት ጋር ባለን ነገር ማንም እሱን
እንዲወቅሰው አልፈልግም።
★ ከልጄ አባት ጋር ተያይዘን ትልቅ ቦታ እንደርስ
ነበር። ግን አልሆነም። አሁንም በጣም ነው
የምወደው ማርያምን።
★ ባለፈው ያንን ቪዲዮ ከሠራሁ በኋላ ተደዋውለናል።
★ ቤተሰቦቼን መርዳት ባለመቻሌ ብዙ ነገር
ተበላሽቷል።
★ እቅዴን ረስቼ የራስ ስሜት ላይ ትኩረት በማድረጌ
ዋጋ አስከፈለኝ።
★ ማርገዜን ከ 4 ወር በኋላ ነው ያወቅኩት።
★ የማስወረድ ሀሳብ በአዕምሮዬ አልመጣም።
ሀጢያት እንደሆነ አውቃለሁ።
★ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ናት ያረጋጋችኝ !።
★ ስልኬን አጥፍቼ ፣ ቤቴን ዘግቼ
ዝም ብዬ ቁጭ አልኩኝ።
★ አልጋው ላይ ሆኜ ቀኑም ጨለማውም ይታየኛል።
★ ቤት ዘግቼ በተቀመጥኩበት ሰዓት የቤት
አከራያችን ቤዚ በሰራተኛዋ ምግብ
ትልክልኝ ነበር።
★ ቤዚ ላርስሽ ብላኝ ነበር።
★ የቤት አከራያችንን ቤዚን ሳላመሰግናት አላልፍም።
ማርያምን ቤዚን በጣም ነው የምወዳት።
★ ባላወራው ፣ ባላስታውሰው ደስ ይለኛል።
ከውስጤ አልወጣም።
★ እርግዝና ውስጥ ሆኜ ነው ራሴን ላጠፋ
የነበረው። ቢላዋ ይዤ ራሴን ያገኘሁበት
ቀን አለ።
★ ቤቴ ውስጥ ፍራሽ አለ። የኪዳነምህረት ስዕለ
አድኖ አለ። እሷን ሳይ ነው የምረጋጋው።
★ 8 ወር ሲሞላኝ እናቴ ጋር ሰቆጣ ሄድኩኝ።
በጣም አስተዋይና ዘመናዊ እናት ነው ያለችኝ።
★ ይሁን እግዚአብሔር የሆነ ነገር ሊያመጣ ፈልጎ
ነው አለችኝ።
★ ጨጓራዬን ሲያመኝ በዩኒቨርሲቲ ምግብ
ነበር የማሳብበው።
★ ሁሉም ሰው ቤተሰብ ጭምር አሪፍ ህይወት
የምኖር ይመስላቸው ነበር።
★ የአባቴ ሚስት ለእኔ እንጀራ እናት አይደለችም።
አራስ ቤት ሆኜ ምንም ነገር እንዳይሰማኝ
አድርጋኛለች።
★ ከዚህ በፊት የሰራሁት አንድ ነጠላ ዜማ አለኝ።
★ ያልጠበኳቸው ትልልቅ ሙዚቀኞች አይዞሽ
ከጎንሽ ነን ብለውኛል።
★ አዲስ ለምሰራው ነጠላ ዜማ ደግሞ
ሙሉ ወጪውን የሸፈነችው
ድምፃዊት ራሄል ጌቱ ናት። አመሰግናታለሁ።
★ ሠይፉ አርቱ ላይ ስለምሰራ ሰርቼ እንድንገናኝ
ነበር የፈለኩት።
ተዋናይት/ድምፃዊት ቤተልሔም ሰለሞንን ለማገዝ
የምትፈልጉ
1000300078803
CBE
ስልክ – 0924-39-01-08
Share ሼር በማድረግ ለደጋግ ሰዎች አድርሱላት !
Bethelhem Solomon Lala
ቤቲ አንቺ ጠንካራ ሴት ወርቅ የሆነ ሙያ አለሽ።
አይዞሽ ሁሉንም ታልፊዋለሽ።
ፋና ላምሮት ላይ የምታሳያቸውን ብቃቶች ከዚህ
በፊት አጋርቼው ስለማውቅ አቅምሽን በደንብ
አውቀዋለሁ። በርቺ !
አክባሪሽና አድናቂሽ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!
