ዶናልድ ትራምፕ ከቬንዚዌላ ነዳጅ በሚገዙ ሃገራ ላይ የ 25 በመቶ ታሪፍ እንደሚጥሉ አስታወቁ

Date:

ትራምፕ እንዳስታወቁት ከቬንዚዌላ ነዳጅ በመግዛት ወደ ሃገሩ በሚያስገባ ማንኛውም ሃገር ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ይጣልበታል ብለዋል፡፡

ትራምፕ በትሩዝ ማህበራዊ ድረገጻቸው ላይ በጻፉት መልዕክት ቬንዚዌላ ከአሜሪካ ጋር እጅግ ጠበኛ ሃገር ነች ስለዚህም ከቬንዚዌላ ላይ ነዳጅ የሚገዙ ሃገራት ከአሜሪካ ጋር በሚኖራቸው የንግድ ልውውጦች ላይ 25 በመቶ ታሪፍ ይጣልባቸዋል ይህም ከ ሚያዚያ 12 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ስፔን ህንድ ሩሲያ ሲንጋፑር እና ቬተናም ከ ቬንዚዌላ ላይ ነዳጅ በመግዛት ከሚታወቁት ውስጥ ናቸው፡፡

እስከ ዛሬ ባለው ራሷ አሜሪካም ከቬንዚዌላ ነዳጅ ስታስገባ የቆየች ሲሆን ባለፈው ጥር ወር ብቻ 8 ነጥብ 6 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ከቬንዚዌላ አስገብታለች፡፡

ባጠቃላይ ከጥር ወር ወዲህ ሁለት መቶ ሁለት ሚሊየን በርሜል ነዳጅ አሜሪካ ከሃገሪቱ ገዝታለች ሲል የዘገበው ዩሮ ኒውስ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...