- አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ
ግብጾች በህዳሴ ግድብ ምክንያት የሀገራቸው አርሶአደሮች እንደሚፈናቀሉ በማስመሰል ዓለምን ሲያስፈራሩ እና ሲያደናግሩ መቆየታቸውን በውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ገለጹ፡፡
አቶ ፈቅአህመድ ከጋዜጣ ፕላስ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የህዳሴ ግድብ አንድ ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሀ ሲይዝ 2 ሚሊዮን የግብጽ አርሶአደር ግማሹ አውሮፓና አሜሪካ ይሰደዳል፤ ግማሹ አሸባሪ ይሆናል በማለት ግብጾች ዓለምን በውሸት ያደናግራሉ፡፡
በተጨማሪም ግድቡ ሲሞላ የአስዋም ግድብ ወደ በርሀነት ይቀየራል የሚል የተሳሰተ እሳቤ ያላቸው መሆኑን አንስተው፤ ግብጾች የሚሰጧቸው አሳሳች ምክንያቶች ኢትዮጵያ ስለውሀ አጠቃቀም ብሎም ስለሌላ ግድብ እንዳታስብ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን አሁን የህዳሴ ግድብ ውሀ ተሞልቷል፤ የአስዋን ግድብም ሙሉ ነው፤ አንድም አርሶአደር አልተሰደደም ትርክቱም ውሸት መሆኑን ዓለም አረጋግጧል ብለዋል፡፡
ግድቡ መገንባቱ ተፋሰሱ ውስጥ በጋራ የምንጠቀምበት ተጨማሪ ውሀ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ጋዜጣ_ፕላስ
በማህሌት ብዙነህ
