በኢ/እ/ፌ ዋና መሥሪያ ቤት የተካሄደው ውይይት የፌዴሬሽኑ እና ማኅበሩን ግንኙነት በማጠንከር የኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገትን በሚደግፉበት፣ በእግር ኳሱ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ብሔራዊ የውዝግብ መፍቻ ተቋምን ማቋቋም በሚቻልበት፣ ማኅበሩ መልካም ተሞክሮዎችን ከሌሎች ሀገራት ተቋማት የሚቀስምበትን ሂደት በማመቻቸት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። በውይይቱ በእግር ኳሱ እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎች በተለይም የተጫዋቾች መብት እና ክለቦች ተጫዋቾችን የሚይዙበት መንገድ ዙርያ ውይይት ተደርጓል።
ክቡር ፕሬዝዳንቱ ተጫዋቾች ለስፖርቱ ዋነኛ እሴት መሆናቸውን ጠቁመው ማኅበሩ የአባላቶቹን አቅም በማሳደግ ዙርያ ጠንክሮ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሁለቱ አካላት ውይይት እግር ኳሱ ወደተሻለ ምዕራፍ እንዲሸጋገር በቅርበት ለመስራት የጋራ ቁርጠኝነት በመግባት ተጠናቋል።
