Home ቢዝነስ ዜና ለአምስት የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች የሥራ ፍቃድ ተሰጠ

ለአምስት የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች የሥራ ፍቃድ ተሰጠ

ለአምስት የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች የሥራ ፍቃድ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፍቃድ መስጠቱን አስታወቀ። ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ለአምስቱ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የስራ ፍቃድ የሰጠኋቸው ተፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸው አረጋግጨ ነው ብሏል። የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ለማስፋፋትና ለማዳበር የሚረዳ ሚና ይኖራቸዋል ብሏል። የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዥ ወዲያውኑ የሚፈጸም (spo† transaction) ብቻ ይሆናል ሲል አስታውቋል። የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለ ጉምሩክ ዴክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት እንደሚችሉ አመላክቷል።እንዲሁም ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ እንደሚችሉ ጠቁሟል። የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎቹ በባንኩ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግባቸው አስታውቋል።