መርስክ የበርበራ ወደብ የጭነት አገልግሎቶችን ለጊዜው አቋረጠ

Date:

የዓለማችን ግዙፍ የመርከብ ድርጅት የሆነው መርስክ ፣ ወደ በርበራ ወደብ የሚደረጉ እና ከወደቡ የሚወጡ አዳዲስ የጭነት ቦታ ማስያዣዎችን ለጊዜው ማቋረጡን በይፋ አስታውቋል።

ኩባንያው ለዚህ አስቸኳይ ውሳኔ ምክንያት የሆነው በመርከብ የጉዞ መርሃ ግብር ላይ የተደረገ ለውጥ መሆኑን የገለጸ ሲሆን፣ ይህም ውሳኔ በተለይ በርበራን እንደ አማራጭ የንግድ በር ለምትጠቀመው ኢትዮጵያ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል።

በቅርብ ዓመታት የበርበራ ወደብ ለኢትዮጵያ ወሳኝ የሆኑ እንደ ማዳበሪያና እህል ያሉ ምርቶችን ለማስገባት ትልቅ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ በመሆኑ፣ የአገልግሎቱ መቋረጥ በቀጠናው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የራሱ ጥላ ማረፉ አይቀሬ ነው።

መርስክ አዳዲስ የጭነት ጥያቄዎችን መቀበል ቢያቆምም፣ ቀደም ብለው የተጫኑ እና በጉዞ ላይ ያሉ ንብረቶች በታቀደው መሠረት መድረሻቸው እንዲገቡ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

በተጨማሪም ድርጅቱ ደንበኞቹ የአቅርቦት ሰንሰለታቸው እንዳይስተጓጎል አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ያሉትን የጅቡቲ፣ የሞቃዲሾ እና የሞምባሳ ወደቦችን እንደ አማራጭ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...