ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የማህበራዊ ሚድያ እንዳይጠቀሙ እገዳ ለመጣል መወሰኑን የዴንማርክ መንግስት አሳወቀ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜት ፍሬድሪክሰን በባለፈው ወር ለፓርላማ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር የህፃናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ እገዳ እንዲጣል ጥሪ አቅርበው ነበር። ይህንን ተከትሎ በዴንማርክ ፓርላማ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ዕቅዱን እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
” ማህበራዊ ሚድያ የልጆቻችንን ጊዜ ፣ ልጅነታቸውን እና ደህንነታቸውን በመስረቅ ላይ ሲሆን እኛም ይህንን በማስቆም ላይ ነን ፤ ይህም የሚደረገው በዲጂታል ዓለም ውስጥ ህፃናትን እና ወጣትቶችን ለመጠበቅ ነው ” ሲሉ የዲጂታል ጉዳዮች ሚኒስትር ካርሎን ስቴጅ ኦልሰን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ የትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ እገዳ እንደሚጣል እና እንዴት እንደሚተገበር በግልፅ አላሳወቁም ፤ ነገር ግን ወላጆች ከ13 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ያሉ ልጆች የተወሰኑ መተግበሪያዎች ለመጠቀም እንዲችሉ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል፡፡
ዴንማርክ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ መጠን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የዕድሜ ገደቦችን ለማስተዋወቅ አንድ ትልቅ እርምጃ እንደምተወስድ ተገልጿል።
#SocialMedia #Denmark
@tikvahethiopia
