የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስረታ 90ኛ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ሩሲያን ጨምሮ የአምስት ሀገራት አየር ኃይሎች የሚሳተፉበት የአየር ትርኢት በቢሾፍቱ ሰማይ ስር ሊቀርብ ነው።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ምስረታ 90ኛ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ፣ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ የሩሲያ፣ የሞሮኮ እና የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይሎች በጋራ የሚሳተፉበት “የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት 2026” ከጥር 15 እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በቢሾፍቱ በድምቀት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አሳውቋል።
ከአየር ትርኢቱ በተጨማሪ “የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ የቻይና፣ የህንድ፣ የአሜሪካና የደቡብ አፍሪካ ግዙፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2026 እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አስታውቋል።
በኤክስፖው ላይ ከ25 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ለዕይታ ያቀርባሉ።
