ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ሽኩቻ ማብቃቱን ገለጸች

Date:



የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ሚኒስትር ዴታ አሊ መሀመድ ኦማር በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባት ፍፃሜ አግኝቷል ብለዋል ።

ይህ የተናገሩት በኳታር፣ ዶሃ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ወቅት ከአል-አራቢ አል-ጀዲድ ጋር ባደረጉት ልዩ ቃለ ምልልስ ላይ ነው።

ኦማር “ክርክሩ አልቋል። የቱርክ መንግስት በአደራዳሪነት ለተጫወተው ሚና እናመሰግናለን። ድርድሩ የተሳካ ሲሆን ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እውቅና እንድትሰጥ እና የግዛት አንድነቷን እንድታከብር ስምምነት ላይ ተደርሷል” ብለዋል ማለታቸውን ዳውን አፍሪካ ዘግቧል።

ይህ ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ የጀመረው በ2016 አጋማሽ  መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ሰነድ    ስትፈራረም ነበር። ስምምነቱ ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን የባህር ዳርቻ ክፍል ለንግድ ወደብ እና ወታደራዊ ካምፕ እንድትጠቀም የሚያስችል ሲሆን፣ በምላሹም ሶማሌላንድን እንደ ገለልተኛ መንግስት እንድትገነዘብ ያደርጋል።

የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ስምምነቱን የአገሪቱን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መጣስ ነው በማለት በጽኑ ተቃውሞ ነበር።

ሚኒስትሩ “እንደ ጎረቤት አገሮች እና የአፍሪካ ህብረት አባላት በጋራ ትብብር ላይ የተመሰረተ ስምምነት ላይ ደርሰናል። ኢትዮጵያ የሶማሊያ ወደቦችን ለንግድ ዓላማዎች መጠቀም ከፈለገች ይፈቀድላታል፣ ነገር ግን እንዲህ ያለው አጠቃቀም በአለም አቀፍ ህግ መመራት አለበት” ሲሉ አስረድተዋል።

ሚኒስትር አሊ መሀመድ ኦማር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ ክምችት የሶማሊያ ልዑክ ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...