የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለአምባሳደሩ እና ልዑካቸው በኢንስቲትዩቱ እየተከናወኑ ስለሚገኙ የቴክኖሎጂ ስራዎች ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ሁለቱ ሀገራት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች በአፍሪካ በኤ.አይ ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የያዘውን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ለማጠናከር በሀገራቱ መሪዎች መካከል ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰው ሀገራቸው በሰው ኃይል አቅም ግንባታ ኢትዮጵያን ለመደገፍ በትኩረት እንደምትሰራበት አጽንኦት ሰተዋል፡፡
ልዑካኑ በኢንስቲትዩቱ የሚገኙትን የሮቦቲክስ ዎርክሾፕ፣ ሾውሩም እንዲሁም የስታርታፕ ማዕከል እና ዩኒፖድን በጉብኝታቸው ወቅት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
