በመዲናዋ ከ1መቶ 22 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በደንብ መተላለፍ ተቀጡ

Date:

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በባለፉት ዘጠኝ የበጀት ወራት 40 መንገዶች ላይ ቁጥጥር ማድረጉን ተናግሯል።

ተደርጓል በተባለዉ ቁጥጥር 1መቶ22 ሺህ 9 መቶ 57 አሽከርካሪዎች የደንብ መተላለፍ ቅጣት የተጣለባቸዉ መሆኑን ገልጿል።

ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከርከሩ የተገኙ ከ80 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች፣ ከተፈቀደው የአልኮል መጠን በላይ ጠጥተው የተገኙ 1 ሺህ 6 መቶ 53 አሽከርካሪዎች ላይ የእርምት እርምጃ ወስጇለሁ ብሏል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት የደህንነት ቀበቶ ሳያደርጉ አገኘኋቸው ያላቸዉን 3ሺህ 66 ደንብ ተላላፊዎች፣በተመሳሳይ የጭንቅላት መከላከያ ቆብ ያላሰሩ 5 መቶ 85 የሞተር ብስክሌተኞችም እንደጥፋታቸው ደረጃ እንዲታረሙ መደረጉን ተናግሯል።

በተመሳሳይ 7 ሺህ 26 አሽከርካሪዎች ስልክ እያነጋገሩ አደባባዮች ላይ እና በመስቀለኛ መንገዶች ላይ ምጽዋት የሰጡ እና ግብይት የፈጸሙ 4 ሺህ 5መቶ ግለሰቦችም በዚህ ደንብ መተላላፍ መቀጣታቸዉ ተገልጿል።

ተቋሙ በዚህ ቁጥጥር ከ37 ሺህ በላይ እግረኞችም በደንብ መተላለፍ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉን አሳዉቋል።

መንገድ አጠቃቀም ዙሪያ በተደረገ ቁጥጥር ማድረጉን በመግለጽ 21ሺህ 2መቶ2 እግረኞች በገንዘብ መቀጣታቸዉን ተቋሙ ገልጿል።

16 ሺህ 6 መቶ 51 እግረኞች የተላለፉትን የመንገድ አጠቃቀም ደንብ በማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ስለመቻሉ አያይዞ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት 7 መቶ 43 መኪኖች በክሬን ተነስተዉ ለትራፊክ ፍሰቱ ምቹ እንዲሆን ስለማድረጉ አሳዉቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...