በምሥራቅ አርሲ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተገለፀ

Date:

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት የካቲት 19 ለ 20 አጥቢያ አንድ ካህን፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለጽሕፈት ቤታችን ከጻፉት ደብዳቤ ስንመለከት እጅግ በከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል።

በመሆኑም በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት በኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመውና የተፈጸመው ዘግናኝና እጅግ አሳዛኝ ግድያዎች የኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችንን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በነጻነት የመኖርና ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን የመፈጸም መብትን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥታት ጉዳዮን በልዩ ሁኔታ መከታተልና የማያዳግም መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው እያሳሰብን የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም የአካባቢው ችግር በመሰረቱ እስከሚፈታ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን።

በመጨረሻም በዚህ ዘግናኝና አሳዛኝ ግድያ ሕይወታቸውን

ላጡ ልጆቻችን እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ
መሆኑን እንገልጻለን።

                     አባ ሳዊሮስ

የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ

ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...