በሶሪያ የተደረሰው ተኩስ አቁም

Date:

ኩርድ መራሹ የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች ከአሊፖ መውጣታቸውን አስታወቁ።

ከማክሰኞ ጀምሮ በሶሪያ ወታደሮች እና በኩርድ  ሀይሎች መካከል በሰሜን እና ምስራቅ  ሶሪያ ከፍተኛ ዉጊያ ተካሂዷል ።

በውጊያው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ሲሰደዱ፣ ከ22 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የኩርድ ሀይሎች በተደረሰው ተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በሶሪያ ሁለተኛ ግዙፍ ከተማ ከሆነችው አሊፖ ለቀው መውጣታቸውን ገልፀዋል ።

የሶሪያ መከለከያ ሀይል ኩርድ መራሹ ከሼክ ማቅሱድ ይዞታው ሸሽቶ ወደ ሰሜን መሄዱን እና የቡድኑ አባላት ምርኮኛ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል ።

አክሎም  በኩርድ ሀይል ቁጥጥር ስር የነበረችውን አሽራፊየህን ነፃ ማውጣቱን ተናግሯል ።

የኩርድ ተዋጊዎችን ወደ ሶሪያ መደበኛ ሰራዊት ለመቀላቀል የተደረገው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ ፣ በአሊፖ ለሳምንት የዘለቀ ዉጊያ መደረጉ የሶሪያን ፖለቲካ ውስብስብ አድርጎት መቆየቱ ይታወሳል።

ፍራንስ 24 ዘግቦታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...

የሽብር ተከሳሹ ካናዳዊው እሱባለው በለጠ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ በነጻ ተሰናበተ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ዜግነት ያለው እሱባለው በለጠ በነጻ ተሰናብቶ...