Home ትምህርት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት በግጭት ከወደሙ 374 ትምህርት ቤቶች አንዱም ተመልሶ አልተሰራም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት በግጭት ከወደሙ 374 ትምህርት ቤቶች አንዱም ተመልሶ አልተሰራም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት በግጭት  ከወደሙ 374 ትምህርት ቤቶች  አንዱም ተመልሶ አልተሰራም

ጥያቄው የተነሳው የትምህርት ሚኒስቴር የዘጠኝ ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በአፋር ክልል ከወደሙ ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መልሶ መገንባት የቻለው 4 ብቻ መሆኑ በፓርላማ ጥያቄ አስነስቷል፡፡

በግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች በፍጥነት የትምህርት ሚኒስቴር እየገነባ አይደለም የሚል ቅሬታ ቀርቦበታል፡፡

አቶ አብዱ ሁሴን የተባሉ የምክር ቤት አባል በሰሜኑ ጦርንት በአፋር ክልል ከወደሙ ከ300 በላይ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መገንባት የተቻለው 4ቱን ብቻ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስቴርን ሪፖርት በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሃላፊነት የወሰደባቸውን ሌሎች ትምህርት ቤቶችን በአፋጣኝ ገንብቶ የመማር ማስተማር ሂደቱ ወደነበረበት እንዲመለስ ቢደረግ ሲሉ የምክር ቤት አባሉ ተናግረዋል፡፡

ፈንቲ ረሱ እና ኪሊበቲ ረሱ በተባሉ ሁለት ዞኖች አማራጭ የሆኑ የማስተማሪ አካባቢ ሌላ ተማሪዎች ሊማሩ የሚችሉት ዛፍ ስር ሆነው ነው፤ ስለዚህ የትምህርት የሚኒስቴር የወሰደውን ሃላፊነት በአግባቡ ተወጥቶ የመማር ማስተማሩ ሂደት ወደነበረበት ቢመለስ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ  ክልል ባለፉት ሶስት ዓመታት በግጭት ምክንያት 374 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፤ እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለማቋቋም ምን እየተሰራ ነው? ሲሉ የትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በሰጡት ምላሽ የአፋሩ ክልል መልሶ ግንባታ በታቀደው ልክ መሄድ ያልቻለው በክልሉ ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

እንዲገነቡ ፍቃድ በተሰጣቸው ተቋራጮች ምክንያት ነው የዘገየው ብለዋል፡፡

የቤኒሻንጉሉ ጉዳይ በተመለከተም የትምህርት ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ በጦርነት የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን ስናይ ያየነው የአማራ እና አፋር ክልሎችን ብቻ ነበር  አሁን ግን በኦሮሚያም በቤኒሻንጉልም በጦርነት የተጎዱትን ለመገንባት እየተሰራን ነው ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/fgnhjgfdfgh/

ሸገር 102.1