Home ዜና በቴሌኮም ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ማጭበርበሮችን የብሔራዊ መታወቂያን በመጠቀም ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ተገለፀ

በቴሌኮም ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ማጭበርበሮችን የብሔራዊ መታወቂያን በመጠቀም ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ተገለፀ

በቴሌኮም ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ማጭበርበሮችን የብሔራዊ መታወቂያን በመጠቀም ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ተገለፀ

በበርካታ ዘርፎች እንደ ቅድመ ሁኔታ እየተጠየቀ የሚገኘው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በቀጣይም በቴሌኮም ዘርፉ ላይ ማጭበርበሮችን ለመከላከል በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ስራዎች መጀመራቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል።

በቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ ሲደረግም የሲም ካርድ ቁጥጥር እና ያለአግባብ በሲም ካርዶች የሚፈፀሙ የብድር ማጭበርበሮችን ለማስቀረት እንደሚረዳ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላት ዳይሬክተር አቶ ሳሚናስ በላይነህ ተናግረዋል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አንድ ማንነትን ለአንድ ግለሰብ የሚሰጥ በመሆኑ በአገልግሎት ሰጪ ማዕከላት ላይ የነበረውን ክፍተት ለመሙላት እንደሚያግዝ እና ተቋማትን እንደሚያስተሳስርም ሃላፊው አንስተዋል።

እንዲሁም በትምህርት፣ በፋይናንስ እና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ፋይዳ ነባር መታወቂያዎችን ተክቶ የሚያስቀር እንዳልሆነ አቶ ሳሚናስ ገልፀዋል ።

እስካሁን ባለውም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ13 ሚሊየን በላይ ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለማግኘት መመዝገባቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።