በአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች አዲስ መመሪያ ላይ የሽግግር ጊዜ ሊሰጥ ነዉ

Date:

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ላይ ሊተገብር ባሰበው አዲስ መመሪያ ዙሪያ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሁለት እና የሦስት ዓመታት የሽግግር ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ።

ሚኒስቴሩ በቅርቡ ባወጣው መመሪያ የአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ካሪኩለም ማለትም የታሪክ፣ የቋንቋ እና የዜግነት ትምህርቶችን እንዲያካትቱ እንዲሁም የተማሪዎቻቸው ስብጥር ቢያንስ 30 በመቶ የውጭ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስገድድ ነው።

ይሁን እንጂ እንደ ዋን ፕላኔት፣ ብሪቲሽ እና ካናዲያን ኢንተርናሽናል ያሉ ታዋቂ ትምህርት ቤቶች መመሪያው በአንድ ጊዜ ተግባራዊ መደረጉ ተማሪዎችና ወላጆች ላይ መስተጓጎል ይፈጥራል በሚል ተቃውሞ አቅርበው ነበር።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈዉ ሳምንት ባደረጉት ውይይት፣ መመሪያው የማይቀየር መሆኑን ቢገልጹም፣ ትምህርት ቤቶቹ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሽግግር ጊዜ ሊፈቀድ እንደሚችል መናገራቸውን የካፒታል ምንጮች ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ አክሎም ትምህርት ቤቶቹ ይዘታቸውን ከሀገሪቱ ካሪኩለም ጋር ቢያቀናጁም፣ የማስተማሪያ ቋንቋቸው ግን እንደቀድሞው በእንግሊዝኛ እንዲቀጥል እንደሚፈቀድላቸው አረጋግጧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...