የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ እንደገለጹት፤ በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት አመት የክረምት የዜግነት አገልግሎት 30 ሺህ 444 የገጠር መምህራን መኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት በትምህርት ዘርፍ የዜግነት አገልግሎት 4420 ቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ጠቅሰው 777 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም መገንባታቸውን ገልጸዋል።
3 ሺህ 382 የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ሥራ መሰራቱን ጠቅሰው በአጠቃላይ 45.6 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሥራ መሰራቱን አስረድተዋል።
ዘንድሮ 2 ሺህ 853 አዲስ ቡኡረ ቦሩ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን እንዲሁም 1 ሺህ 577 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት መታቀዱን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በበጀት አመቱ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ 66.4 ቢሊየን ብር የሚገመት የክረምት የዜግነት አገልግሎት ሥራዎችን ለመስራት ታቅዷል ብለዋል። በክረምት የዜግነት አገልግሎት የክልሉ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው፡፡
