
ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፥ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚነንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የትግራይ ህዝብ ለቀጣይ አንድ ዓመት ስልጣኑ የሚራዘመውን የጊዚያዊ አስተዳደሩን የሚመራ ፕሬዜዳንት እንዲጠቁም አስመልክቶ ያወጡትን መልዕክት ” የተናጠል ውሳኔና ተግባር ” ሲል ተቃውሟል።
” የፕሪቶሪያ ሥምምነት ከተፈረመ ሁለት ዓመት ተኩል ሆኖታል ” ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ” ስምምነቱ በሙሉነት ተተግብሮ ትግራይ በህዝብ የተመረጠ መንግስት ሊኖራት ይገባ ነበር ” ብሏል።
” የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በሙሉነት ያልተተገበረው የፌደራል መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀምና አተገባበር በተከተለው የተሳሳተ አካሄድና ፓለቲካዊ ቀውስ እንዲፈጠር በመስራቱ ነው ” ሲልም ክስ አሰምቷል።
” በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 3 መሰረት ተዋዋይ ወገን ሌላውን በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ በፕሮፓጋንዳ ማጥቃት ይከለክላል ይሁን እንጂ ይህንኑ የስምምነቱ አካል በፌደራል መንግስት በተደጋጋሚ እየተጣሰ ነው ” ብሏል።
” የፌደራል መንግስት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መንፈስና ይዘት በወጣ አካሄድ አግባብነት በሌላቸው 359/1995፤ ደንብ 533/2015 ህግና አዋጆች እንዳሻው እየወሰነ ይገኛል ” የሚል ወቀሳም አቅርቧል።
” የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አንቀፅ 10 የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግስት መግባባት እንዲቋቋም ያዛል ” ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ” የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ውሳኔ መወሰን አይችልም ” ብሏል።
” ህወሓት ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ከስልጣን ማስነሳቱ ተከትሎ ፤ ጀነራል ታደሰ ወረደ ፕረዚደንት እንዲሆኑ ማእከላይ ኮሚቴ ወስኖ የኢትዮጵያ መንግስት ተቀብሎታል ” ያለም ሲሆን ” ይህንን ወደ ጎን በመተው በጠቅላይ ሚንስትሩ የተናጠል ውሳኔ በሚያስመስል መልኩ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚጥስ አካሄድ ተቀባይነት የለውም ” ሲል ገልጿል።
” የፌደራል መንግስት ህዝብን ከሚጎዱ ግልፅ ተግባራት በመቆጠብ ዘላቂ ጥቅምና የጋራ ሰላም በሚያረጋግጡ ተግባራት እንዲያተኩር ጥሪ እናቀርባለን ” ያለው የደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ” የተናጠል ውሳኔዎች እንዲቆሙ ” ብሏል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle@tikvahethiopia