በጅቡቲ ነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናል ጥገና አለመከናወኑ የነዳጅ ጭነቱ እንዲቀንስ ሆኗል

Date:

ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው ነዳጅ ጅቡቲ በሚገኘው የሆራይዘን ነዳጅ ማጠራቀሚያ ተርሚናል በኩል መሆኑን ተከትሎ፤ የማጠራቀሚያ ተርሚናሉ ጥገና ባለመከናወኑ የነዳጅ ጭነቱ እንዲቀንስ ማድረጉን የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታውቋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እስመላለም ምህረቱ ለአሐዱ እንደገለጹት ከሆነ፤ ችግሩን ለመፍታት ተጨማሪ 2 የነዳጅ ተርሚናሎችን እንዲኖሩ ከጅቡቲ መንግሥት ጋር ውይይት እንደተደረገ ይገኛል።

በጅቡቲ ከውጭ የሚገባው ነዳጅ በሆራይዘን ተርሚናል በኩል ከመርከብ ወርዶ ወደ ተሽከርካሪዎች እንደሚጫን ያስረዱት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖው በምስረታው ጊዜ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እንደነበርና አሁን ያለው ፍላጎት 4 ነጥብ 2 እንደደረሰ ተናግረዋል።

ነዳጅ ማጠራቀሚያው ከ20 ዓመት በፊት የተቋቋመ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፤ ረዘም ላለ ጊዜ የነዳጅ ማውረድ እና ጭነት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ተርሚናል በመሆኑ በፖምፕ እና የሲስተም ክፍተቶች በመኖራቸው በነዳጅ የጭነት አገልግሎቱ ላይ አልፎ አልፎ ጭነቱ እንዲቀንስ ምክንያት ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ነዳጅ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓጓዝበት መንገድ ለተሽከርካሪዎች ምቹ አለመሆኑን በማንሳት፤ በአሽከርካሪዎች ዘንድ ቅሬታ እንደሚነሳም ለአሐዱ ተናግረዋል።

አክለውም ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከተደረገ በኃላ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚደረግ የነዳጅ ዝውውር እና የነዳጅ  ሽያጭ ለነዳጅ አቅርቦቱ ላይ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...

ከ8 ሺህ በላይ ጥንታዊ የብራና ጽሑፎችን እና ሰነዶችን ወደ ዲጂታል ተቀየሩ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት ከተለያዩ ተቋማት፣...

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...