ባርሴሎና በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ወደ ስፖቲፋይ ካምፕ ኑ ስታዲየም እንደሚመለስ የክለቡ ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ አስታውቀዋል።
የባርሴሎናው ስፖቲፋይ ካምፕ ኑ ስታዲየም ባለፉት አመታት በእድሳት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
“ በሚቀጥለው የውድድር አመት መጀመሪያ ጀምሮ ወደ ካምፕ ኑ እንመለሳለን “ ሲሉ ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ አረጋግጠዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሁኔታዎች በጥሩ ሁኔታ ከሄዱ ባርሴሎና በየአመቱ የሚያዘጋጀውን የ ሁዋን ጋምፐር ዋንጫ ጨዋታ በካምፕ ኑ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
የዘንድሮው የ ሁዋን ጋምፐር ዋንጫ ጨዋታ በካምፕ ኑ ስታዲየም ነሐሴ ወር መጀመሪያ ላይ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
@Tikvahethsport
