ቬሮኒካ አዳነ በናይጄሪያ አሳዛኝ ነገር ገጠማት

Date:

“የሚያሳዝን ቀን ነበር በናይጄሪያ ያሳለፍኩት”

ኢትዮጵያዊቷ የሙዚቃ ኮከብ ቬሮኒካ አዳነ በመላው አፍሪካ ትልቅ ግምት የሚሰጠውን የ9ኛው የአፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት (AFRIMA) በአሸናፊነት አጠናቃለች። ቬሮኒካ በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው በዚህ ደማቅ ስነ-ስርዓት ላይ፦“The Best Artist, Duo or Group in African Traditional Music” በሚለው ዘርፍ አህጉራዊ ተፎካካሪዎቿን በመብለጥ ድልን ተቀዳጅታለች።

ከሽልማቱ በስተጀርባ ያለው አሳዛኝ ክስተት ምንድን ነው?

ድምፃዊቷ በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለምን አልታየሽም ለሚሏት ደጋፊዎቿ በማህበራዊ ትስስር ገጿ በሰጠችው ምላሽ በናይጄሪያ የገጠማት ነገር አስከፊ እንደነበር እንዲህ ስትል ገልጻለች

Afrima አዋርድ ላይ ብዙ ሰው ለምን አላየንሽም የሚል ጥያቄ እየመጣብኝ ነው… ምክንያቱን መናገር ይኑርብኝ አይኑርብኝ ባላውቅም በጣም የሚያሳዝን ቀን ነበር በናይጄሪያ ያሳለፍኩት፤ ብቻ ማሸነፌ በቂ እና ከበቂ በላይ ስለነበር እሱ ብቻ እንዲገን ስለፈለኩ ዝምታን መርጫለሁ። ለዛም ነው ማንም ሰው አቀባበል እንዲያደርግልኝ ያልፈለኩት ” ብላለች።

ቬሮኒካ በቆይታዋ የገጠማትን ዝርዝር ችግር ባትገልጽም፣ ሀገሯን በድል በማስጠራት ግን ዳግም ታሪክ ሰርታለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አዲስ አበባ ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ...

የቴሌኮም ኦፕሬተሮች የ5 በመቶ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ክፍያን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱት ሁለቱም የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ማለትም ኢትዮ ቴሌኮም እና...

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ...

አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት ይገባል

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አፍሪካ ቋሚ ውክልና...