የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከብራዚሉ ክለብ ፍሉሚኔንሴ ጋር ያደረገውን የክለቦች አለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አዲሱ ፈራሚ ጇ ፔድሮ ሁለቱንም ማስቆጠር ችሏል።
ቼልሲ በውድድሩ ካደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች አምስቱን ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፏል።
ቼልሲ በፍፃሜው የፊታችን እሁድ የሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂን አሸናፊ የሚገጥሙ የሆናል።
ሌላኛው ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሸት 4:00 ላይ ሪያል ማድሪድ እና ፒኤስጂ ይፋልማል።
