አሜሪካ ማምሻውን ባወጣችው መግለጫ የሶማልያ መንግስት በዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ ጥቃት በማድረስ የአሜሪካ ድጋፍ የሆነ 76 ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታ መወሰዱን ኮንኗል።
መልሶ እርዳታ ሊጀመር የሚችለው የሶማሊያ መንግስት ለህገወጥ ለተግባሩ ሃላፊነቱን ወስዶ ተገቢውን እርማት ካደረገ ብቻ መሆኑን መግለጫው አክሏል።
የፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሶማሊያ መንግስት ምቹ አለመሆኑ ይገልፃል።
ባለፉት ቀናት ትውልደ ሶማሊያውያን በአሜሪካ አንዳንድ ግዛቶች በተለይ በአሜሪካ መንግስት በሚደገፉ የህፃናት እና አዛውንት ማቆያ ስራ ጋር በተገናኘ ማጭበርበር ላይ ተሳትፈዋል በሚል በሪፐብሊካን መር ማእከላዊ መንግስት ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ይገኛል።
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ የሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ተወካይ አምባሳደር አቦከር ዳሂር ኡስማን ስማቸው እየተነሳ ነው።
