አቢሲኒያ ባንክ በሁሉም  ቅርንጫፎቹ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

Date:

ይህ የወረቀት አልባ ልዩ የባንክ አገልግሎት ዘመናዊ የባንክ አሠራሮችን እንዲይዝ ተደርጎ በአዲስ መልክ በተዋቀረው ራስ ልዩ ቅርንጫፍ  ነው በዛሬው ዕለት ተመርቆ ስራ የጀመረው ።

የአቢሲኒያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፤በዚህ አዲስ አሠራር ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ገንዘብ ለማስተላለፍ፣ ለማስገባትና ለማውጣት፣ ሒሳብ ለመክፈት ያስችላል ብለዋል።

አገልግሎቱ የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀም በመሆኑ፣ ጊዜ የሚወስዱ የአሠራር ሂደቶችን በማስወገድ የባንኩን አገልግሎት ለማሳደግ እንደ ሚያገለግልም ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

ለአጠቃቀም እንዲመች እንግሊዝኛን ጨምሮ በተለያዩ አገራዊ ቋንቋ  እንደ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማሌኛ፣ ትግርኛ፣ አፋርኛ እና ሲዳምኛ አቅርበናል ብለዋል።

የንግዱ ማህበረሰብ እንዲሁም ግለሰቦች በቅርንጫፍ ውስጥ ወረፋ መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው፤ እንዲሁም ቴክኖሎጂው ላይ በተገጠሙ ዘመናዊ መሳሪያዎች ያለ መብራትና  ኢንተርኔት አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ(ዶ/ር) ፤ባለፉት 30 ዓመታት በባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ  አዳዲስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ረገድ አቢሲኒያ ባንኩ ትልቅ አበርክቶ እያደረገ ነው ብለዋል።

የፋይናንስ ዘርፍን በተቻለ መጠን ተወዳዳሪና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የማህበረሰቡን ጊዜ፣ድካምና ጉልበት ሊቆጥቡ የሚችሉ አሰራር ማስተዋወቅና ተግባራ ማድረግ ግድ ይላልም ሲሉ  የብሔራዊ ባንክ ገዢው ተናግረዋል።

ከውጭ ከሚገቡት ባንኮች ጋር በእኩልነት ለመስራት የአሰራር ደረጃን ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት አሁን የብሔራዊ ባንክ ገዢው  ማሞ(ዶ/ር)፤ባንኮች እያደረጉት ባለው ጥረት የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ አገልግሎቱ በቅርቡ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ይሆናሉም ብለዋለ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...