አንጀሊና ጆሊ ከ8 ዓመታት የሕግ ፍልሚያ በኃላ አዲስ ህይወት ፍለጋ

Date:

ለብዙዎች ሎስ አንጀለስ የዝናና የሀብት ከተማ ናት። ለታዋቂዋ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ ግን፡ ላለፉት ስምንት ዓመታት በግዷ የኖረችበት፡ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የታሰረችበት ከተማ ነበረች።

አሁን ግን፡ ያ የህግ ሰንሰለት ሊበጠስ ጥቂት ሲቀረው፡ ጆሊ ከዚህ “የወርቅ እስር” ለመውጣትና አዲስ የህይወት ምዕራፍ ለመጀመር መዘጋጀቷን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

የጆሊ የሎስ አንጀለስ “እስራት” የተጀመረው፡ ከቀድሞ ባለቤቷ ብራድ ፒት ጋር በገቡት ከባድ የፍቺ እና የልጆች የማሳደግ መብት ክርክር ነበር።

ለስምንት ዓመታት የዘለቀው ይህ አሰቃቂና አደባባይ የወጣው የህግ ፍልሚያ፡ ባለፈው ታህሳስ 2024 በስምምነት ተጠናቋል።

የጆሊ ጠበቃ እንዳሉት፡ “አንጀሊና ደክማለች፡ ነገር ግን ቢያንስ ይህ የህግ ፍልሚያ አንድ ምዕራፍ በማለፉ እፎይታ ተሰምቷታል።”

የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት፡ ጆሊ የሎስ አንጀለስ መኖሪያ ቤቷን ለሽያጭ ለማቅረብ እየተዘጋጀች ነው።

እቅዷም ግልጽ ነው፤ መንትያ ልጆቿ ኖክስ እና ቪቪዬን በሚቀጥለው ዓመት 18 ዓመት ሲሞላቸው፡ ከተማዋን ለቅቃ ወደ ውጭ ሀገር መሄድ።

ተዋናይቷ ከዚህ ቀደም በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ፡ “በሎስ አንጀለስ የኖርኩት በፍቺዬ ምክንያት ግዴታ ስለሆነብኝ ነው” ብላ ነበር። “ነገር ግን ልጆቼ 18 ዓመት ሲሞላቸው፡ ከተማዋን መልቀቅ እችላለሁ።”

የጆሊ ውሳኔ፡ ከቦታ ለውጥ የዘለለ ጥልቅ ትርጉም አለው። እርሷ የምትፈልገው፡ ለትልቁ ቤተሰቧ “ግላዊነት፡ ሰላም እና ደህንነት” ነው።

በአንድ ወቅት “በዓለም ዙሪያ ያገኘሁት አይነት ሰብዓዊነት (humanity)፡ እዚህ ባደኩበት ከተማ ውስጥ የለም” ስትል የሆሊውድን ህይወት ተችታለች።

አንድ የቅርብ ምንጭ እንደሚለው፡ “ልጆቿ፡ አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ ስልጣንና ጥቅም ስላላቸው፡ የእነርሱ ድምጽም ሆነ ህመማቸው ዋጋ እንደሌለው እያዩ ነው ያደጉት።”

አሁን ጆሊ የምትፈልገው፡ ከዚህ ሁሉ ጫና ርቆ የሚገኝ ሰላማዊ ህይወት ነው።

በመጨረሻም አንጀሊና ጆሊ ከህይወቷ ትልቁን የህመም ምዕራፍ ከዘጋች በኋላ፡ ቀሪ ህይወቷን በራሷ ፍላጎት ልትመራ ቆርጣለች።

ብዙ ጊዜዋን የመጀመሪያ ልጇን ማዶክስን ባሳደገችበት ካምቦዲያ እንደምታሳልፍና በዓለም ዙሪያ የሚገኙትን ቤተሰቦቿን እንደምትጎበኝ ተናግራለች።

ይህ ጉዞ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ የሚደረግ ሳይሆን ከህመም ወደ ፈውስ፡ ከእስራት ወደ ነጻነት የሚደረግ ታላቅ ጉዞ ነው። አሁን አንጀሊና ጆሊ አዲስ አበባ ናት።

(ዘ-ሐበሻ ዜና)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...