‘ኢራን በአሜሪካ ዲፕሎማሲ ላይ እምነት የላትም’

Date:

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኢራን ባለሥልጣናት የድርድር ዕቅዳቸውን መላካቸውን እየገለጹ ባለበት ጊዜ ኢራን በአሜሪካ ላይ እምነት እንደሌላት ገለጸች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ ለሕንዱ ጋዜጣ ‘ኢንዲያ ቱዴይ’ በሰጡት ቃለ ምልልስ “ማንም በአሜሪካ ዲፕሎማሲ ላይ ዕምነት ሊጥል አይችልም” በማለት ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል።

ጨምረውም “የአሜሪካንን ዲፕሎማሲ በተመለከተ ኢራን በጣም መጥፎ ልምድ አላት” በማለት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ድርድሮች እየተካሄዱ ሁለት ጊዜ ጥቃት እንደተፈጸመባት በማብራራት ድርጊቱን “የዲፕሎማሲ ክህደት” ብለውታል።

ቃል አቀባዩ እንዲሁም “በአሜሪካ እና በኢራን መካከል እየተካሄደ ያለ ድርድር እንደሌለ” አጽንኦት በመስጠት አስተባብለው፤ በአሁኑ ጊዜ የኢራን ጦር ኃይሎች ትኩረታቸውን ያደረጉት “የአገሪቱን ግዛት በመከላከል” ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

አንድ ወር ሊሞላው የተቃረበውን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሚያካሂዱት ጦርነትን ለማብቃት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአምስት ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀምጠው የድርድር ነጥቦችን ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

አስካሁን ግን ከኢራን በኩል ስለድርድሩ በይፋ የተባለ ነገር ካለመኖሩ በተጨማሪ የተለያዩ የአገሪቱ ባለሥልጣናት የተጀመረ ንግግር እንደሌለ እየተናገሩ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...