በኢትዮጵያ ፖሊስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የወንጀል ምርመራ አካዳሚ ተከፈተ

Date:

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ ኣዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ ፖሊስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የወንጀል ምርመራ አካዳሚ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ መከፈቱን ዛሬ በይፋ አብስረዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አካዳሚውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር አካዳሚው በምርመራ ሂደት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናትና ምርምር በመለየት፣ የቴክኒክና የታክቲክ የምርመራ አቅምን ይበልጥ ፕሮፌሽናል ለማድረግና የፖሊስን የኦፕሬሽን አቅም በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል።

በተለይም የሳይበር፣ የፋይናንስ፣ የሙስናንና ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያስችል የላቀ እውቀት ያላቸው ስፔሻላይዝድ የሆኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያስችልም ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አስገንዝበዋል።

የወንጀል ምርመራ አካዳሚው የሚሰጠው አገልግሎት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን፣ ከሀገራችን የፖሊስ ተቋማት ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል አቅም እንደሚኖረው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ክቡር ታምራት ሙሉጌታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ እንዲህ ዓይነት የላቀ አካዳሚ በጥቂት ሀገራት ብቻ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ አካዳሚው ዪኒቨርስቲው በዲፕሎማና በዲግሪ በጀንራል የምርመራ ዕውቀት የሚያስመርቃቸውን ባለሙያዎች በታክቲክና በቴክኒክ ምርመራ ስፔሻላይዝድ እንዲያደርጉ ታስቦ የተቋቋመ መሆኑን ገልፀዋል።

በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሊሳ አብዲሳ በበኩላቸው፤ በክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ሀሳብ አመንጭነት ተጀምሮ ዛሬ በይፋ የተከፈተው የወንጀል ምርመራ አካዳሚ በሀገራችን የፖሊስ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑን ገልፀው አካዳሚው የመርማሪዎችን አቅም በእጅጉ የሚያሳድግና ለሌሎች የሀገራችን የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከላትም እንደ ሞዴል ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል አስረድተዋል።

ምንጭ:-  የፌደራል ፖሊስ ማህበራዊ ገፅ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...