ኢትዮጵያ ለኬንያ በቀን 265 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እያቀረበች ነው ተባለ

Date:

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በተፈራረሙት የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሰረት ለኬንያ በቀን 265 ሜጋ ዋት ኃይል እየቀረበ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢትዮ-ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ኮንቨርተር ጣቢያ ምስራቅ አፍሪካን በኃይል ለማስተሳሰር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገልጿል።

በጣቢያው የጥገናና የኦፕሬሽን ባለሙያ አቶ መኮንን ካሴ እንደተናገሩት ጣቢያው ከወላይታ ሶዶ ቁጥር ሁለት የማከፋፈያ ጣቢያ በአራት ባለ 400 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመሮች ተቀብሎ፣ 12 ኮንቨርተር ትራንስፎርመሮችን እና 1ሺህ 680 ታሪስተሮች(thyristors) ተጠቅሞ ኃይል የሚያስተላልፍ ነው።

ጣቢያው 2000 ሜጋ ዋት ኃይል የመሸከም አቅም ባላቸው በሁለት ፖሎች እና ከኢትዮጵያ እስከ ኬንያ በተዘረጋ 1ሺህ 60 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመር አማካኝነት ኃይል እያስተላለፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከኬንያ ጋር ባለው የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሰረት በአሁኑ ወቅት በቀን 18 ሰዓት ማለትም እስከ ምሽት 6 ሰዓት 200 ሜጋ ዋት እንዲሁም ከዚያ በኋላ በሚኖረው ቀሪ 6 ሰዓት ደግሞ 65 ሜጋ ዋት ኃይል እየቀረበ ይገኛል ብለዋል።

ጣቢያው በስምምነቱ መሠረት እየጨመረ የሚሄደውን የኃይል አቅርቦት እና ወደ ታንዛኒያ ኃይል ለማስተላለፍ የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት የሚያስችል አቅም እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚደረጉ የኃይል ሽያጭ ስምምነቶችን ተከትሎ አስተማማኝና ኃይል በማስተላለፍ ለአህጉራዊ የኃይል ትስስር መሳለጥ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከባድ ሙስና የተከሰሱትን 4 ተከሳሾችን፤ ፖሊስ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ቀረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ የ'ይፈለጋሉ" ማስታወቂያ የወጣባቸው...

ስለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ውጥረት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ...

የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ...

ፔንታጎን የእስራኤል ስለላ እንደሚያሳስበው ተገለጸ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፔንታጎን እስራኤል ከፍተኛ ልዑኮችን ጨምሮ የአሜሪካ...