እስራኤል የአሜሪካን የተኩስ አቁም ሃሳብ መቀበሏን አስታወቀች

Date:

የእስራኤል መንግሥት በዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን የተኩስ አቁም ሃሳብ መቀበሉን ገለፀ።

ዛሬ ማለዳ ላይ ባወጣው መግለጫ “እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተጣሰ ጠንካራ ምላሽ ትሰጣለች” ብሏል።

የእስራኤል መንግሥት በኢራን ላይ ያደረሰው ጥቃት “ዓላማውን” ማሳካቱን በመግለጽ የተኩስ አቁም ሃሳብን ተቀብያለሁ ብሏል።

እስራኤል አክላም ኢራን በኒውክሌር ጦር መሳሪያ እና በባለስቲክ ሚሳኤሎች የደቀነችውን “ሁለት ፈጣን የኅልውና ስጋት” አስወግጃለሁ ብላለች።

በተጨማሪም እስራኤል “በወታደራዊ አመራር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም በርካታ የኢራን መንግሥት ዒላማዎችን አውድሜያለሁ” ብላለች።

የእስራአል መንግሥት መግለጫ በመቀጠል የእስራኤልኃይሎች በመጨረሻውቀን በወሰዱት እርምጃ “በቴህራን ማዕከላዊ ክፍል በሚገኝ የመንግሥት ዒላማዎችን በመቶዎች የሚቆጠሩ የባሲጅ አባላትን” ማስወገዳቸውን ገልጿል።

የባሲጅ ታጣቂዎች የኢራን መንግሥት ተቃውሞን ለማፈን የሚጠቀምባቸው ሚሊሻዎች ናቸው።

መግለጫው አክሎም በዚሁ ጥቃት “ሌላ ከፍተኛ የኒውክሌር ሳይንቲስትን ተገድሏል” ብሏል።

“እስራኤልፕሬዝዳንት ትራምፕን እና አሜሪካን በመከላከያ ላደረጉት ድጋፍ እና የኢራንን የኒውክሌር ስጋት ለማስወገድ ላሳዩት ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል” ሲል መግለጫው ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...