ትራምፕ ኢራን እና እስራኤል በተመሳሳይ ጊዜ ሰላም እንደሚፈልጉ እንደጠየቋቸው ተናገሩ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል እና ኢራን “በተመሳሳይ ጊዜ ማለት ይቻላል ሰላም [እናውርድ] አሉኝ” ሲሉ ጽፈዋል።
በዚህ ጊዜ “ጊዜው አሁን እንደሆነ አወቅኩ” ሲሉ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ለጥፈዋል።

ሁለቱ አገራት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በመጥቀስ “ዓለም እና መካከለኛው ምሥራቅ እውነተኛዎቹ አሸናፊዎች ናቸው። ሁለቱም አገራት ወደፊት ታላቅ ፍቅር፣ ሰላም እና ብልጽግናን ያያሉ” ብለዋል።

ኢራንም ሆነች እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ስለመደረሱ ቤእፋ ያሉት ነገር የለም።

ቴህራን እስራኤል ኢራንን መደብደቧን ካቆመች እርሷም ሚሳዔሎቿን ማስወንጨፍ እንደምታቆም ገልጻለች።

ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ ሁለቱ አገራት “ በርካታ የሚያገኙት ነገር አለ።እንዲሁም ከፍትህ እና ከእውነት መንገድ ከራቁ የሚያጡትም አለ” ብለዋል።

ልጥፋቸውን ሲያጠናቅቁም የእስራኤልና የኢራን የወደፊት ዕጣ ፈንታ “ያልተገደበና በታላቅ ቃል ኪዳን የተሞላ ነው። እግዚአብሔር ሁለታችሁንም ይባርክ!” ብለዋል።

BBC Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...