ከአሜሪካ መንግስት ድጋፍ ያገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መረጃቸውን እንዲያቀርቡ ተጠየቁ

Date:

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመዝግበው ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) እና ከአሜሪካ መንግስት ሌሎች ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ በመቀበል በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ሲያከናውኑ የነበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መረጃቸውን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንዲያቀርቡ ተጠየቁ።

ይህ ጥሪ የአሜሪካ አስተዳደር በአገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ እያደረገ ያለውን የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ ወይም ማቆም ጋር በተያያዘ ለቀጣይ ተግባራት አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ ስለሆነም USAIDን ጨምሮ ከማንኛውም የአሜሪካ መንግስት ተቋም የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ ሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለሚመለከተው ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣነሰ ሪፖርት እንዲያደርጉ በጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠቱ ለማወቅ ተችሏል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...

ከአሜሪካ ጋር የሚኖረው “የጨዋታው ሕግ ተቀይሯል፤ የተመጣጠነ ምላሽ ዘመን አብቅቷል

ኢራን ከአሜሪካ በኩል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው ተመጣጣኝ የአጸፋ ምላሽ...

የ2.5 ቢሊየን ብር ግዙፍ ፕሮጀክት በአታ ለማርያም ገዳም በመስከረም ወር የመሠረት ድንጋይ ሊያኖር ነዉ

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ የታዕካ ነገሥት...

የዲቪ ዕድለኞች የማመልከቻ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ ተወሰነ!

የአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት በዲቪ ሎተሪ አመልካቾች የማመልከቻ ሂደት...