የሦስቱ ተቋማት የዲጂታል ኢንሹራንስ ምን ይዞልን መጣ

Date:

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፣ ሉሲ ኢንሹራንስ አ.ማ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ በጋራ በመሆን «አጋር» የተሰኘ ለኢንሹራንስ ተጠቃሚዎች ፣ ለሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች እና ለደሞዝተኞች የሚሆን የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡


በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የኢንሹር-ቴክ ፕሮዳክት አጋር ዲጂታል የኢንሹራንስ ደንበኞች ወደ ኢንሹራንስ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ ሆነው ስልካቸውን
ብቻ በመጠቀም ለንብረታቸው የመድን ሽፋን ዋስትና መግዛት የሚችሉበት ሙሉ በሙሉ ዲጂታል እና
ከወረቀት ንክኪ የፀዳ አገልግሎት መሆኑ በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የተገለፀ ሲሆን ማንኛውም ግለሰብም
ሆነ ድርጅት የካቻ የስልክ መተግበሪያ ላይ በመመዝገብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ተነግሯል።


በተጨማሪም የመድን ሽፋን ዋስትና የሚገዙ ደንበኞች የዓረቦን ክፍያቸውን ለመክፈል የሚገጥማቸውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል ዲጂታል የብድር አገልግሎት የተመቻቸ እንደሆነ ሲገለፅ ይህ አገልግሎት ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች የመድን ሽፋን ለመግዛት የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ መጠን በሙሉም ሆነ በከፊል በብድር የሚያገኙበት መሆኑ ተገልጿል።

በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች በተበደሩት መጠን ልክ ብድራቸውን በ1 ወር፣ በ3 ወር፣ በ6 ወር እና በ9 ወር መክፈል የሚችሉ ሲሆን ደንበኞች በተመቻቸላቸው የጊዜ ገደብም ብድሩን መክፈል
መቻላቸው ለኢንሹራንስ ሽፋን የአረቦን ክፍያ ለመክፈል የሚያጋጥመውን የፋይናንስ ችግር ከመቅረፍ
ባሻገር የዲጂታል አገልግሎት አይነት ከመሆኑ አንፃር የተገልጋዩን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስና
የኢንሹራንስ ክፍያን በወቅቱ ካለመክፈል የሚመጡ ችግሮችን አስቀድሞ ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑ
ተብራርቷል ፡፡


በተጨማሪም በእለቱ “አጋር ለሹፌሮች” የተሰኘ የዲጂታል ብድር አገልግሎት ይፋ ሲሆን አገልግሎቱ
በተለምዶ “ራይድ” ተብለው ለሚጠሩ የሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች ድንገተኛ ለሆነ የተሸከርካሪ ጥገና እና
መለዋወጫ ግዢ ፍላጎት ወይም አሽከርካሪዎች ለሚያጋጥሟቸው የተለያዩ አስቸኳይ የፋይናንስ ፍላጎቶች በየትኛውም ቦታና ሰዓት የእጅ ስልክን ብቻ በመጠቀም ለህብረተሰቡ አገልግሎት ከመስጠት ሳይስተጓጎሉ
ባሉበት ቦታ ሆነው የአጭር ጊዜ ብድር ማግኘት የሚያስችል ዘመናዊ የዲጂታል ብድር አገልግሎት እንደሆነ ሲጠቆም እንዲሁም “አጋር ለደሞዝተኞች” የተሰኘው አገልግሎት ሰራተኞችን የደሞዝ መደረሻ የገንዘብ ፍላጎትን ለማርካት የተዘጋጀ የቅድመ ደሞዝ የብድር አገልግሎት እንደሆነ ሰራተኞችም ከክፍያ ቀናቸው በፊት ለሚገጥማቸው የገንዘብ እጥረት የወር ደሞዛቸውን የተወሰነ ክፍል ያለምንም ማስያዣ በብድር
እንዲያገኙ የሚያስችል የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት መሆኑ ታክሏል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...