የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የአፍሪካንዊያንን የመልማት ህልም ዳግም ከፍ ያደረገ ነው

Date:

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች  ዙሪያ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው የታላቁ  የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበራት  ዲፕሎማሲያዊ  ግንኙትት ላይ ተጨማሪ ግብዓት ሆኗታልም ሲሉ  ሰፋ ያለ ማብራሪያ አድርገዋል።

የግድቡ መጠናቀቅ ከኢትዮጵያውን አልፎ ለአፍሪካዊያን አዳዲስ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በአለም አቀፍ ደረጃ  የእድል በር  የከፈተ አጋጣሚ  ተገኝቶበታል ብለዋል።

በዚሁ መግለጫ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ  የአየር ንብረት ጉባዔ ላይ ማብራሪያ የሰጡት ቃል አቀባዩ ከ25 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ገልፀዋል። በጉባዔው የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ ሰነዶች ተካተዋልም ተብሏል።

በጉባዔው መጨረሻም የአፍሪካ የአየር ንብረት ፈንድ እንዲቋቋምም ከስምምነት መደረሱን የውጭ ጉዳይ መግለጫ አስታውቋል።

የአፍሪካ ካረቢያን ማህበረሰብ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ፤ በዚሁ ጉባዔ አዳዲስ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደተመሠረተም ተጠቁሟል።

በተለይም ባርባዶስ ከኢትዮጵያ ጋር የስራ እድል ለዜጎች ለመስጠት ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር መስማማታቸው  ተመላክቷል።

የአፍሪካ ካረቢያን ጉባዔ ተሳታፊዎች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መመረቁ ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ አርአያነቷን ያስመሠከረችበት ነው ማለታቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም በቀጣዩ ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) 80ኛ ጉባዔውን በኒውዮርክ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።  

በዚሁ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን የሚያስከብሩ አጀንዳዎችን ይዛ ተሳታፊ እንደምትሆን አምባሳደር ነብያት ይፋ አድርገዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...