በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ድንገተኛ ሕልፈት ምክንያት ሐዘናችንን ሐዘናችሁ በማድረግ ላፅናናችሁን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። የአርቲስት ነፃነት ቤተሰብ ወደመጡበት ሃገር ከመመለሳቸው በፊት ለቤተሰቡ የቅርብ ሰዎች ሕጋዊ ውክልና ሰጥተዋል ።
በመሆኑም ፣ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህን የተመለከቱ ማናቸውንም የሥራ ጉዳዮች እንዲከታተሉና እንዲያስፈጽሙልን በማለት አቶ አስናቀ ንጉሴን የወከልን መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
ከአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ስም ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጉዳይ ቢኖራችሁ አቶ አስናቀ ንጉሴን ማነጋገር እንደምትችሉ እንገልፃለን።
ከዚህ በተጨማሪም ፣ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ እና ቤተሰቡን የተመለከተ የትኛውንም ዓይነት መረጃ ማግኘት ስትፈልጉ ተወካዩን በአካል ወይም በስልክ ማነጋገር ትችላላችሁ። በተለይ የሟችንም ሆነ የቤተሰቡን ስም የሚያጠፉ እንዲሁም ክብር የሚያጎድፉ ስሁት ትርክቶችን በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይዘዋወሩ ለማስቀረት እንዲቻል ፣ ትክክለኛ መረጃዎችን ከሕጋዊ ተወካያችን ብቻ እንዲቀበሉ ፤ የተወካያችንን ቃል ብቻ ጠቅሰው እንዲጠቀሙ እንጠይቃለን።
ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ የሟችንም ሆነ የቤተሰቡን መልካም ስም የሚያጎድፍ ስሁት የፈጠራ ታሪክ ማሰራጨት በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑንም እናስታውሳለን።
ስልክ :- 0903886870 ( አስናቀ ንጉሴ )
