የአለም ጤና ድርጅት ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች ላይ ጭማሪ እንዲያደርጉ ጠየቀ

Date:

ድርጅቱ በምርቶቹ ላይ የሚደረገው የታክስ ጭማሪ የ50 ሚሊየን ሰዎችን ህይወት ያድናል ብሏል።

የአለም ጤና ድርጅት በ2035 ሀገራት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች ላይ የሚጥሉትን ታክስ በ50 በመቶ ለመጨመር እንዲችሉ የሚገፋፋ ንቅናቄ ጀምሯል።

ድርጅቱ ‘3 by35’ ሲል የሰየመው ኢንሼቲቭ ገቢ ከማስገኘት በተጨማሪ መከላከል የሚቻሉ ገዳይ በሽታዎችን በመቀነስ የሚሊዮኖችን ህይወት ይታደጋል ብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የብዙሃኑን ህይወት እንደሚቀሙ በመጥቀስ እነዚህን ምርቶች ከመጠቀም በሚመጡት እንደ የልብ ህመም ፣ ካንሰር እና ሌሎችም  ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አሁን ላይ 75 በመቶ የሰው ልጅ የሞት ምክንያት እየሆኑ ነው ሲልም ገልጿል።

የታክስ ጭማሪው የምርቶቹን ፍጆታ በመቀነስ ለመንግስታት ተጨማሪ ገቢ ያመጣል የሚለው ድርጅቱ ወደ ትግበራ ለመግባት ጊዜው አሁን ነው ብሏል።

ንቅናቄው በሚቀጥሉት 10 አመታት በሲጋራ፣ አልኮል እና የስኳር መጠጦች የሚጣልን የኤክሳይዝ ታክስ በመጨመር 1 ትሪሊየን ዶላር ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን የተገኘው ገንዘብም ለሀገራት ልማት እና የጤና ተደራሽነት ይውላል ተብሏል።

ከ2012-2022 ባሉት 10 አመታት 140 ሀገራት በምርቶቹ ላይ የታክስ ጭማሪ እንዳደረጉ ሲመላከት ደቡብ አፍሪካ እና ኮሎምቢያ በጥሩ ምሳሌነት ተነስተዋል።

ድርጅቱ አንዳንድ ሃገራት እነዚህን ምርቶች ለሚያመርቱ ኢንዱስተሪዎች ማበረታቻ ይሰጣሉ በሚል ሲተች ሃገራቱ እንደዚህ አይነት ማበረታቻዎችን እንዲያነሱም ጠይቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...