የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያን ከፋይዳ ጋር በ‘ኦንላይን’ የሚያስተሳስር አዲስ አሠራር እየተዘረጋ ነው

Date:

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአካል መሄድ ሳይጠበቅባቸው የነዋሪነት መታወቂያቸውን ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር የሚያስተሳስሩበት የ‘ኦንላይን’ አሠራር እየተዘረጋ እንደሆነ የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የወሳኝ ኩነት እና የነዋሪነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጥጋቡ ሹመይ፤ አዲሱ የ ‘ኦንላይን’ የአሰራር ስርአት በቅርቡ ባንኮች አካውንትን ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር ከጀመሩት አሠራር ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሲሆን፥ ደንበኞች በያሉበት ሆነው አገልግሎቱን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

አሁን ላይ በ90 የከተማዋ ወረዳዎች ከፋይዳ ጋር የተሳሰረ ደኅንነቱ የተጠበቀ አዲስ መታወቂያ የመስጠት ሥራ በስኬት እየተከናወነ ቢሆንም፥ እስካሁን መታወቂያ ማስተሳሰር የሚቻለው በአካል ብቻ እንደሆነ ኃላፊው ጠቁመዋል።

ይህ ዲጂታል አሠራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቀላሉ ተደራሽ እንደሚያደርግ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

አቶ ጥጋቡ አክለውም፥ በቅርብ ወራት ውስጥ ማንኛውም የአዲስ አበባ ነዋሪ ወደ ወረዳ መዋቅሮች ሳይንከራተት የሚፈልገውን አገልግሎት በሙሉ ባለበት ሆኖ መጨረስ የሚችልበት እድል መፈጠሩን አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...