የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ብሄራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ 7ኛ ጨዋታውን አድርጓል።
በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፈርኦኖቹ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ዋልያዎቹን አሸንፈዋል።
የፈርኦኖቹን የማሸነፊያ ግቦች ሞሀመድ ሳለህ እና ኦማር ማርሙሽ በመጀመሪያው አጋማሽ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።
የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን የምድብ 8ኛ ጨዋታውን ጳጉሜ 4 ከሴራሊዮን ጋር ያከናውናል።
ምድቡን ግብፅ በ19 ነጥብ ስትመራ ቡርኪነፋሶ በ14፣ ሴራሊዮን በ9፣ ጊኒ ቢሳው በ7፣ ኢትዮዽያ በ6 እንዲሁም ጅቡቲ በ አንድ ነጥብ ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ድረጃ ይዘዋል።
