የኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት የ240 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ለስድሰት ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የ240 ሚሊየን ዩሮ (የ32.3 ቢሊየን ብር) የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል ፡፡

የድጋፍ ስምምነቱ በዋናነት የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የግብርና ስራዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በመጠቀም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ልማትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን በማጠናከር በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን አስተዳደርና አካታችነትን በማሻሻል መረጋጋትን ለማስፈን የማያግዝ ነው ።

እንዲሁም በግጭት የተጉዱ የጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስና እንዲሁም ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል ፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት ድጋፉ የግሉ ዘርፍን የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲጨምር ለማገዝ፣ የታክስና ጉምሩክ ስርዓቱን ለማዘመን፣ የግብርና፣ጤናና ትምህርት አገልግሎትን ለማሳደግ የሚያስችል ም ነው ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...