የኢትዮጵያ አየር መንገድ የብሪክስ ሀገራትን የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ እንደሚሠራ ገለፀ

Date:



ይህ የተገለፀው በዛሬው እለት በተከፈተው የመጀመሪያው የኢትዮጲያ የአቪዬሽን ፎረም ላይ ነው።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ስብሰባ በዘርፉ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር፣ የልምድ ልውውጥ እና ለጋራ ችግሮች የጋራ መፍትሄዎች እንደሚፈለጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አየር መንገዱ የብሪክስ ሀገራትን የአየር ትራንስፖርት በማሳደግ ረገድ የበኩልን ሚና የሚጫወትበትን መንገድ እያጤነ እንደሆነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

“በብሪክስ ማሕበረሰብ ውስጥ ንግድ ለመጨመር እንቅስቃሴ አለ። በብሪክስ ህብረት ኩባንያዎች ሊተባበሩባቸው ከሚችሉባቸው መስኮች ውስጥ አንዱ የአየር ትራንስፖርት ኢንዱስትሪ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በብሪክስ ሀገራት መካከል የአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን በማሳደግ ረገድ ሊጫወተው የሚችለውን ሚና በተመለከተ ጥናት እያካሄደ ነው። ይህንን ከሌሎች የብሪክስ አባላት ጋር በመሆን መዳሰሳችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...