የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልዕክት

Date:

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

ምክር ቤቱ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እና የኢማን እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል።

​​ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሙስሊሞች ዘንድ በታላቅ ድምቀትና መንፈሳዊ ስነ-ስርዓት የሚከበር ታላቅ በዓል መሆኑን ጠቅሷል።

በዓሉ ነቢዩ ኢብራሂም ለአላህ ያሳዩትን ፍጹም ታማኝነት፣ መስዋዕትነት እና ትዕግስት የምናስታውስበት በመሆኑ፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እነዚህን እሴቶች ጠብቆ ሊያከብረው እንደሚገባ አሳስቧል።

​የአረፋ በዓል ከስግደትና ከተክቢራ ስነ-ስርዓቶች በተጨማሪ፣ ህዝቡ እርስ በእርስ የሚተሳሰብበት፣ ሀብታም ደሃውን የሚጠይቅበት እና የማህበረሰብ አንድነት ይበልጥ የሚጠነክርበት የደስታ ወቅት መሆኑም ተገልጿል።

​​የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የአረፋን በዓል ሲያከብሩ የእስልምናን መርሆዎች መሰረት በማድረግ መሆን እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳስቧል።

  • ​አቅመ ደካሞችን፣
  • ​ወላጅ አልባ ህጻናትን፣
  • ​ህመምተኞችን፣
  • ​ጠያቂና ረዳት የሌላቸውን አዛውንቶች እና የተቸገሩ ወገኖችን በመጠየቅና በመርዳት በዓሉን በጋራ ማክበር እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

​በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ሙሉው ማህበረሰብ በበዓሉ ደስታ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) አደራ በማስታወስ መልዕክት አስተላልፏል።

​​ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ስደት የተከናወነባት፣ የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች በሰላምና በደህንነት የተስተናገዱባት የፍትህ ምድር መሆኗን የጠቀሰው መግለጫው፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ይህንን ታሪካዊ አደራ በመጠበቅ ለሀገር ሰላምና አንድነት ዱዓ ሊያደርግና በጋራ ሊቆም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቷል።

​በማጠቃለያውም፣ በሀገሪቱ በሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ማህበረሰቡ በንቃትና በነጻነት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል።

ህዝቡ ድምጹን ሲሰጥና ውሳኔ ሲያስተላልፍ በሰላማዊ መንገድ፣ በብስለት፣ አርቆ በማሰብ እና ለሀገር በሚበጅ መልኩ መሆን እንዳለበትና ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ እያንዳንዱ ዜጋ የዜግነት ድርሻውን መወጣት እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...