የዝንጀሮ ፈንጣጣ( Mpox) አሁንም አለም አቀፍ የህብረተሰብ የጤና ስጋት ነው

Date:

ድርጅቱ በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር መጨመርን ተከትሎ ለአራተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ኮሚቴ ስብሰባ ሲያደርግ የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በበሽታው የሚያዙ ሰዎች መጨመር የዓለም አቀፍ የህብረተሰብ የጤና ስጋት መስፈርትን ያሟላል ብለዋል።

ዳይሬክተሩ በሽታው በተለይ በምዕራብ አፍሪካ በእጅጉ እየተስፋፋ መሆኑን በመግለፅ ከአፍሪካ ውጪ ወደ ሌሎች አህጉራትም መዛመት መጀመሩን አንስተዋል።

ድርጅቱ፥ የድጋፍ ማነስ በሽታውን ለመቆጣጠር ፈተና እንደሆነበትና ዓለም አቀፍ ምላሽ እንደሚያስፈልግም ገልጿል።

በአፍሪካ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ17 ሺ ያለፈ ሲሆን ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከፍተኛውን ቁጥር ትይዛለች።

በበሽታው ባለፈው ሳምንት ከተመዘገቡት ተጠቂዎች ውስጥ 53 በመቶዎቹ ከሴራሊዮን ናቸው ተብሏል።

በሀገራችን ኢትዮጵያም ግንቦት 17 ቀን 2025 ዓ.ም በበሽታው የተያዘ ሰው በሞያሌ አከባቢ መገኘቱ ይፋ ከሆነ በኋላ  ያለፈ የመጀመሪያ ሰው ማስመዝገቧ ይታወሳል።

እስከ ሰኔ 2 ድረስ ባለው ጊዜም 84 የላብራቶሪ ምርመራዎቾን በማድረግ 18 ሰዎች መያዛቸውንና የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

@TikvahEthMagazine

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...