የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ለማብቃት የቀረበው የሰላም ዕቅድ ላይ ከዩክሬን ባለስልጣናት ጋር የሚደረገው ውይይት ውጤታማ ነው፤ ነገር ግን ተጨማሪ ስራን ያሻል አሉ- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ
በዩክሬን አዲስ የብሄራዊ ፀጥታ ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ የተመራ ልኡክ በአሜሪካ ፍሎሪዳ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ እንዲሁ በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዊትኮፍ በዚሁ በትራምፕ የቀረበው የሰላም ዕቅድ ላይ ለመምከር በመጪው ሳምንታት ወደ ዩክሬን ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባለስልጣናቱ በዋነኝነት በዶናልድ ትራምፕ በቀረበው ባለ 28 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ላይ ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የሰላም ዕቅዱ ለሩሲያ ያደላ ነው በማለት ዩክሬንና የአውሮፓ ህብረትን ማስቆጣቱ ይታወሳል፤
ዩክሬን ጦርነቱን ስለምታቆምበት መንገድ ብቻ አይደለም ሉአላዊነቷንና የረዥም አመት ብልፅግና ጉዞዋን የምታረጋግጥበት መንገዶች ላይ ተወያይተናል፤ ነገር ግን ተጨማሪ የቤት ስራዎች አሉብን ብለዋል ማርኮ ሩቢዮ
የዩክሬን አዲሱ ተደራዳሪ ልዑክ መሪ ሩስተም ኡሜሮቭ ከውይይቱ ኋላ አሜሪካ ታደምጠናች፣ ትደግፈናለች፣ ከጎናችን ናትም ብለዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
