Home ልዩ ልዩ ዜና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለ1216 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለ1216 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ  ለ1216 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት መጪውን የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ1 ሺህ 216 ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል።

በክልሉ ባሉ ማረሚያ ቤቶች በሕግ ፍርድ አግኝተው ሲታረሙና ሲታነጹ ከቆዩ ታራሚዎች መካከል የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡት ወስጥ የይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ተገልጿል።

የይቅርታ ተጠቃሚዎቹ በማረሚያ ተቋሙ በነበራቸው ቆይታ ስለመታረማቸው፤ ስለመታነጻቸውና ስለመልካም ባህሪያቸው በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ተቋማት በቂ ማረጋገጫ የተሰጣቸው ስለመሆኑ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።