ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የወባ መድኃኒት መውሰድ ለተለያየ ችግር ይዳርጋል

Date:

በሐኪም ያልታዘዘ የወባ መድኃኒትን መውሰድ የተለያዩ ጉዳቶችን እንደሚያስከትል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የወባ በሽታ አምጪ ጥገኛ ተኅዋስ ዝርያ ልየታ ሳይደረግና የሕክምና መመሪያ በሌለበት የወባ መድኃኒት መጠቀም÷ ከመድኃኒት መጠን፣ የአወሳሰድ ጊዜና ዓይነት ጋር በተያያዘ ችግር ስሚያስከትል ከመድኃኒቱ የሚጠበቀውን ውጤት ማግኘት እንደማይቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ የፀረ-ወባ መድኃኒቶችን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መጠቀምም መድኃኒቱን የሚቋቋሙ የወባ ጥገኛ ዝርያዎች እንዲፈጠሩ በማድረግ ወደፊት የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም አስቸጋሪ ሁኔታ ያስከትላል፡፡ ከሐኪም ትዕዛዝ ውጭ የሚወሰዱ የወባ መድኃኒቶች ግለሰቡ ከሚወስዳቸው ሌሎች መድኃኒቶች ጋር አሉታዊ መሥተጋብር ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ይህም ጎጂ የጎንዮሽ ጉዳት እንዲከሰት ወይም የሕክምናው ውጤታማነት እንዲቀንስ ስለሚያደርግ፤ የወባ በሽታ ያለበት ሰው መድኃኒት በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ ሕክምናውን መከታተል እንደሚገባው ይመክራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

የእግር ጉዞ ማድረግ የጀርባ ሕመም መጠንን ይቀንሳል

በቀን ለ30 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የጀርባ ሕመምን እንደሚቀንስ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥናት መረጋገጡን የጤና መረጃዎችን የሚያጋራው ላንሴት መፅሔት በቅርቡ አስታውቋል፡፡ ለሕመሙ ከሚሰጡ ውድ ሕክምናዎች ባልተናነሰ የእግር ጉዞም ፍቱን መድሃኒቱ ነው፡፡ የጀርባ ሕመም በዓለም ላይ ከ800 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን እንደሚያጠቃም ነው ተጠቆመ ሲኾን የእግር ጉዞ ሁሉም ሰው ሊከውነው የሚችል እና  ወጪን የማይጠይቅ ነው ያለው ጥናቱ በተለይም ሕመሙን ተከትሎ የሚመጡ ወጪዎችን ማዳን እንደሚስችልም ነው ያስታወቀው። የእግር ጉዞ ለልብ ሕመም፣ ጤናማ ለኾነ የሰውነት ክብደት፣  አጥንት ማጠንከርን ጨምሮ ሌሎችም ተጨማሪ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ዘገባው ያትታል።

የምጥ መርፌና አገልግሎቱ

በተፈጥሯዊ መንገድ ምጥ አልመጣ ሲል ወይም በተፈጥሯዊ መንገድ ከሚመጣበት ጊዜ በፊት መዉለድ አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ልጁ በምጥ መርፌ እንዲወለድ ይደረጋል። ይህ የሚኾነው መቼ ነው? 

  • በእርግዝና ወቅት የሚያጋጥሙ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፤
  • የእንግዴ ልጅ ከማህጸን ግድግዳ መላቀቅ፤
  • ካለጊዜዉ የሚከሰት የእንሽርት ዉሃ መፍሰስ፤
  • ከጊዜዉ ያለፈ እርግዝና፤
  • የጽንስ መቀንጨር፤
  • የጽንስ ሞት፤ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ምክንያቶች ሲኖሩ ሃኪምሽ በምጥ መርፌ እንትወልጂ ሊደረግ ይችላል።

ሂደቱ ምን ይመስላል?

በመጀመሪያ የጽንሱ እንዲሁም የእናትየው ጤንነት ከተረጋገጠ በኋላ የማህጸንሽ ሁኔታ በምርመራ በማረጋገጥ፤ በምጥ መርፌ እንድትወልድ ቢደረግ ወሊዱ ምን ያህል ስኬታማ ሊኾን ይችላል የሚለዉ ይረጋገጣል። ከዚያም በግሉኮስ ዉስጥ የምጥ መርፌዉ ተቀላቅሎ በሃኪም መጠኑ እየተስተካከለ ይሰጣል። የጽሱ የልብ ምት፣ እንዲሁም የእናትየው አጠቃላይ የጤና ሁኔታ በየጊዜዉ ቼክ እየተደረገ ይመዘገባል።

ዶ/ር አድማሱ ለዕላጎ

የጨቅላ ሕጻናት ቢጫ መኾን

የጨቅላ ሕጻናት ቢጫ መኾን እስከ 97% የሚኾኑ ጤነኛ ኾነዉ የተወለዱ ሕጻናት ላይ ሊከሰት ይችላል። ይህም የሚከሰትበት ምክንያት ሕጻናት ገና እንደተወለዱ የዉጭዉን ዓለም ለመላመድ ሰዉነታቸዉ ላይ በሚከሰቱ ለዉጦች ምክንያት ብዙ ፊታልሄሞግሎቢን ቢሊሩቢን የተባለዉን ቢጫ የሚያደርግ ኬሚካል ስለሚለዎጥ ይህንንም ለማብላላት ጉበታቸዉ ጊዜ ስለሚፈልግ ነዉ። ነገር ግን አንዳንድ ሕጻናት በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ሰዉነታቸው ቢጫ ሊኾን ይችላል፡፡ ይህም በጊዜዉ ሕክምና ካላገኘ እስከ አእምሮ እድገት ዉስንነት ድረስ የሚያደርስ ከፍተኛ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

ቶንሲል ምነቱና በሽታው

ቶንሲል በአፋችን የኋላ ግድግዳ  በቀኝ እና በግራ በኩል የሚቀመጡ ጠቃሚ እና ተፈጥሮአዊ እጢዎች ናቸው። ቶንሲል ጥቅም አለው፡፡ በአፍና በአፍንጫ የሚገቡ ተዋህስያንን አጣርቶ ወደ ሳንባ እንዳይገቡ ያስቀራል። የበሽታ መከላከያ ወታደሮችን (antibodies) በማምረት የሰውነት በርን ከጠላት መከላከል የቶንሲል ሥራ ነው፡፡ ቶንሲል እና እንጥል አንድ አይደሉም፡፡ እንጥል (Uvula) በአፋችን የኋላ ግድግዳ መሀል ላንቃ ላይ የሚንጠለጠል አካል ነው።

የቶንሲል ኢንፌክሽን/ ሕመም (tonsillitis) ምንድነው?

ከአቅም በላይ በኾነ ባክቴርያ ወይም ቫይረስ መወረር እና የመቆጣት ባህሪ ማሳየት የቶንሲል ኢንፌክሽን ያስከትላል።

የሕመሙ ምልክቶች

  • ትኩሳት፣
  • ለመዋጥ መቸገር ሕመም፤
  • የምግብ ፍላጎት መቀነስ፤
  • ራስ ምታት፤
  • የአፍ መጥፎ ሽታ፤
  • የአንገት ንፍፊት እብጠት፤
  • ማንኮራፋት ፣
  • አልፎ አልፎ የድምጽ መቀየር (መነፋነፍ)

በተለምዶ የቶንሲል ሕመም ሲኖር ቦታው ላይ በሚኖሩ ለውጦች/ የሰዉነት መቆጣት ምክንያት እንጥል ወረደ በሚል ሰበብ እንጥልን ማስቧጠጥም ኾነ ማስቆረጥ በፍፁም አይመከርም፡፡

ፃን ልጅ እንዴት ሊይዘው ይችላል?

  • ተመሳሳይ ችግር ካለበት ልጅ በትንፋሽ ጠብታ ወይንም በትንፋሽ ጠብታ በተበከለ እጅ ንክኪ፤

መፍትሔ

  • የሕመም እና ትኩሳት ማስታገሻ መድሃኒት፤
  • እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ ጸረ ባክቴሪያ መድሃኒት፤
  • በቂ ፈሳሽ ማሶሰድ እና ረፍት ማስደረግ፤
  • የውሃ እንፋሎት ማጠን፤
  • ሞቅ ያለ የብርቱካን ጭማቂ ማጠጣት፤ በቶንሲል የተያዘው ልጅ ሌላ ልጅ እንዳያስይዝ መድሀኒቱን ከጀመረበት ጀምሮ ለ24 ሰዓት ከት/ቤት ማስቀረት፤

ዶ/ር ሀና ሊሻን (በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር)

አዲስ የተወለዱ ሕጻናት ላይ ሁሉም ቤተሰብ ሊያያቸው የሚገቡ ነገሮች

  • አንድ ጨቅላ ህጻን እንደተወለደ የሰውነቱ ቆዳ ና የአይኑ ነጭ ክፍል ቢጫ የሚሆን ከሆነ
  • ጨቅላው ህጻን እንደተወለደ ሽንቱን እና ሰገራውን ከ2 ቀን በላይ ማውጣት ካልቻለ
  • ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ተደጋጋሚ የማስታወክና ከጡት ወተት ውጪ የተቀየረ ሀሞት የሚመስል አይነት ትውከት ከለው
  • ሆድ መነፋት፣ ማልቀስ፣ ጡት አልጠባም ካለ እና ትኩሳት ካለው
  • ማንቀጥቀጥ ፣ የጭንቅላት መጠን በፍጥነት መጨመር እና አይን ጥቁሩ ክፍል ወደ ላይ መገልበጥ ነገሮች ካሉ
  • የሰገራ መውጫ ቀዳዳ ከሌለ እና ሴቶች ላይ በብዛት ከሽንት ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣ ከሆነ
  • እናት በዉል የማታውቀውን መድሀኒት የምትወስድ ከሆነ

ዶክተር አድማሱ ለዕላጎ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...