ዶናልድ ትራምፕ ቤንያሚን ኔታንያሁን በነጩ ቤተመንግሥት ለመቀበል ቀጠሮ ይዘዋል

Date:

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ ሳምንት ጁላይ 7 የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን በዋይት ሀውስ ተቀብለው እንደሚወያዩ ተገልጿል።

ሁለቱ መሪዎች በኢራን፣ በጋዛ፣ በሶሪያ እና በአጠቃላይ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የትራምፕ አስተዳደር ከእስራኤል መንግሥት ጋር ያለው ግኑኝነት የጠበቀ ሲሆን፤ በጋዛ ያለውን ጦርነት ማስቆም እና በሃማስ እጅ ያሉ ቀሪ ታጋቾችን ማስለቀቅ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ተቀዳሚ ዓላማ ነው ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት ተናግረዋል።

በፈረንጆቹ ኦክቶበር 7 ቀን 2023 የጀመረው የጋዛው ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ አሜሪካ እየሠራች ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ጦርነቱ በሚቆምበት ዙሪያ ሁለቱ መሪዎች ውይይት ያደርጋሉ ማለታቸውን የዘገበው ሮይተርስ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...