ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር 27ኛ ዓመት በዓሉን አከበረ

Date:

ምስረታውን ነሐሴ 17 ቀን 1990 ዓ.ም ያደረገው ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር “ወባን በእኛ ሀብት፣በእኛ እውቀትና ጉልበት እናጠፋለን” በሚል መሪ ቃል 27ኛ ዓመት ምስረታውን አክብሯል።

የጎጃም አካባቢን ትኩረት አድርጎ የተነሳው ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ በ10 ክልሎች ላይ ሌሎች ሶስት ድርጅቶችን አቅፎ በወባ ላይ ትኩረት ያደረገ ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛል።

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር በ10 ክልሎች በሚገኙ 222 ወረዳዎች ፕሮጀክት ለመተግበር ዝግጅቱን አጠናቆ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቋል።

ጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር በአሁኑ ጊዜ 260 ሺ አባላት ያሉት ሲሆን በቀጣዮቹ ዓመታት የማህበሩ አባላት ወደ 1 ሚሊየን ለማድረስ እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ሲሉ የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር መስራች እና ሰብሳቢ አበረ ምህረቴ ተናግረዋል።

ሁሉም ሰው በዓመት 1200 ብር ለፀረ ወባ ማህበር የገንዘብ መዋጮ በማድረግ እና አባል በመሆን ተረባርበን ወባን ማጥፋት አለብን ሲሉ አበረ ምህረቴ ጥሪ አቅርበዋል።

ጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር በ10 ክልሎች በሚገኙ ከፍተኛ የወባ ጫና ባለባቸው 222 ወረዳዎች “ትምህርት ቤት እና ማህበረሰብ አቀፍ ማህበራዊ የባህሪ ለውጥ የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስ በኢትዮጵያ”  የተሰኘ ፕሮጀክት ለመተግበር ዝግጅቱን አጠናቆ በይፋ ስራ መጀመሩን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...