ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው

Date:



ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ  ” በትግራይ በጠበንጃ የሚመራ የፓለቲካ ሀይል ስልጣን ላይ ተቀምጧል ” ሲል ክስ አሰማ።

ህወሓት ከተፈናቃዮች ሳይቀር በማስገደድ ወርሀዊ የፓርቲ መዋጮ እየጠየቀ ነው ያለው ፓርቲው በእንዳስላሰ-ሽረ የተፈናቃዮች የማቆያ ማእከል የሆነውን በማስረጃ አቅርቧል።

በማቆያ ማእከሉ የነበሩት የ6 ልጆች አባት ተፈናቃይ በህወሓት የፓርቲ  ወርሃዊ ክፍያ እንዲከፈሉ ይጠየቃሉ ይላል ፓርቲው።

አባትየው ” እኔ የፓርቲ አባል አይደለሁም ፤ ብሆንም በዚህ ወቅት የመክፈል አቅም የለኝም ” በማለት እንደመለሱ ገልጿል።

” የፓርቲ አባል አይደለሁም ወርሃዊ መዋጮ አልከፍልም ” ያሉት አባት በህወሓት አባላት በፕላስቲክ የተሰራ ቤታቸው ፈርሶ ከመጠለያ ማእከሉ እንዲባረሩ መደረጋቸው ፓርቲው አሳውቋል።

ፓርቲው በትግራይ ህዝብ ጫንቃ በጠበንጃ የሚያዝ የፓለቲካ ሀይል ተጭኗል ቢልም ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ የክልሉ ግዛታዊ አንድነት ሳይረጋገጥ ምርጫ መካሄድ የለበትም ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia            

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...