ለረጅም ዓመታት የኢራንን የስለላ መዋቅር በበላይነት ሲመሩ የቆዩትና በሀገሪቱ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበሩት የቀድሞው የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኃይል የስለላ ኃላፊ ሆሴን ታኢብ፣ ከእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ወንጀል በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተዘግቧል።
በአይሪሽ ታይምስና በኢራን ኢንተርናሽናል ዘገባዎች መሠረት ለከፍተኛው የደኅንነት ባለሥልጣን መታሰር እንደ ዋነኛ ምክንያት የተጠቀሰው፣ በቅርቡ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸማቸው ከ20 ደቂቃዎች በፊት ሆሴን ታኢብ ከሀገሪቱ ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ “ታምሜአለሁ” በሚል ሰበብ በድንገት አቋርጠው መውጣታቸው ነው።
ይህ ድርጊታቸው ስለ ጥቃቱ አስቀድመው መረጃ እንደነበራቸውና ከጠላቶቻቸው ጋር ሳይተባበሩ እንዳልቀረ ከፍተኛ ጥርጣሬን የፈጠረ ሲሆን፣ ለዓመታት ለሥርዓቱ ታማኝ የነበሩት ታኢብ በዚህ መልኩ መጠርጠራቸው በቴህራን የስለላ መረብ ውስጥ ትልቅ ድንጋጤን ፈጥሯል።
