አርሰናል ሲያሸንፍ ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ

Date:

በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል ብራይተንን ሲያሸንፍ ፣ ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር አቻ ተለያይቷል።

በአሜክስ ስታዲየም ብራይተንን እየገጠመው አርሰናል 300ኛ ጨዋታውን ባደረገው ቡካዮ ሳካ ግብ 1ለ0 አሸንፏል።

በኢትሃድ ስታዲየም ኖቲንግሃም ፎረስትን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን 2ለ2 አጠናቋል።

ሲቲ በአንቷን ሴሜንዮ እና ሮድሪ ግቦች በሁለት አጋጣሚ የመምራት እድል ቢያገኝም ውጤቱን አላስጠበቀም።

የመውረድ ስጋት ያለበት ፎረስት በሞርጋን ጊብስ ዋይት እና ኤሊዮት አንደርሰን ግቦች ነጥብ ተጋርቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ አንድ ጨዋታ እየቀረው ከአርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ሰፍቷል።

በሌላ ጨዋታ ቼልሲ ወደ ቪላ ፓርክ አቅንቶ አስቶንቪላን 4ለ1 አሸንፏል። ጆአኦ ፔድሮ ሀትሪክ ሲሰራ ፣ ኮል ፓልመር ሌላኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ዳግላስ ሊውዝ የአስቶንቪላን ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ነው። ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ48 ነጥብ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።

ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ፉልሃምን 1ለ0 በመርታት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።

ክሪሲዬንሶ ሰመርቪል የዌስትሃምን የድል ግብ አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ አርሰናል :- 67 ነጥብ
2️⃣ ማንችስተር ሲቲ 60 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

ቅዳሜ – ማንስፊልድ ከ አርሰናል ( ኤፌ ካፕ )

ቅዳሜ – ኒውካስል ከ ማንችስተር ሲቲ ( ኤፌ ካፕ )

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ብቻ ከ12ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ

በሱዳን የሚገኘው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ...

ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት...

የኢራን ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ምጣኔ ኃብት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው የኢራን...

የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የ፵ ቀን መታሰቢያ ጥሪ

​"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው!" (ምሳሌ ፲፥፯)​በሕይወትና በቃል ትምህርታቸው ብዙዎችን...