ለመድኃኒትነት የሚውሉ 867 እጽዋት ተለይተው ተመዘገቡ

Date:



በኢትዮጵያ ከሚገኙ እጽዋት መካከል ለመድኃኒትነት የሚውሉትን በጥናት በመለየት 867 የእጽዋት ዝርያች ወደ ዘረ-መል ባንክ ማስገባቱን የኢትዮጵያ ብዝኃ ሕይወት ኢኒስቲትዩት አስታውቋል።

በኢኒስቲትዩቱ የመድኃኒት እፅዋት ተመራማሪ እና ቴክንሽያን አቶ ቢኒያም ጣሳው “በኢትዮጵያ ከ7 ሺሕ በላይ እጽዋት ለባህላዊ ሕክምና አገልግሎት እየዋሉ ነው ተብሎ ይገመታል” ያሉ ሲሆን፤ እስከ አሁን ፈዋሽነታቸው በጥናት ተረጋግጦ የተመዘገቡት 867 መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህም ምዝገባ እና ጥበቃ ከተደረገላቸው እጽዋት መካከል 400 የሚሆኑት፤ ዝርያቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢኒስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ የባህል ሕክምና አዋቂዎች ማህበር ጋር በመሆን፤ ለመድኃኒትነት የሚውሉ የእጽዋት ዝርያዎችን የመለየት፣ ምዝገባ የማከናወን እንዲሁም ዝርያዎቹን የማብዛት ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

የጥናት እና የምዝገባ ሂደቱ አሁንም በሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ኃላፊው፤ ወደፊት ተጨማሪ እጽዋት እዚህ ዝርዝር ውስጥ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

ፈዋሽ እጽዋት በሚለው ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት እጽዋት መካከል፤ ቀበርቾ፣ ኮሰሌ፣ ግራዋ፣ ዝግባ፣ ድንገተኛ፣ ዳማ ከሴ፣ አሪቲ፣ ጤናአደም እና መሰል ሀገር በቀል እጽዋት እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።

ከእጽዋት ጥናት እና ምዝገባው በተጨማሪ ማኅበረሰቡ በጥንቃቄ እንዲጠቀምባቸው የማስተማር ሥራዎች መሰራት እንዳለባቸው ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...